የሀገር ውስጥ ዜና

የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎችን ተደራሽነትና አቅም ለማሳደግ በትኩረት መስራት ይገባል

By Melaku Gedif

November 24, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎችን ተደራሽነትና አቅም ለማሳደግ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ተጠባባቂ አምባሳደር ፈርዲናንድ ቮን ቬይሄ፡፡

ኦምኒ አትዮጵያ የተሰኘው ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ከጀርመን መንግስት በጂአይዜድ በኩል በተደረገ ድጋፍ በሚዲያ ልማት ላይ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረትም ላለፉት 16 ወራት ከ27 እስከ 30 ለሚደርሱ በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ የማሕበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረውን የአቅም ግንባታ ሥልጠና አጠናቅቋል

በመድረኩ አምባሳደር ፈርዲናንድ ቮን ቬይሄን ጨምሮ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

አምባሳደር ፈርዲናንድ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በኢትዮጵያ የማሕበረሰብ ራዲዮ ጣቢያዎች በመረጃ የታነጸ ዜጋ ለመፍጠር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ጉልህ ነው፡፡

ስለሆነም የማሕበረሰብ ራዲዮ ጣቢያዎችን አቅምና ተደራሽነት ለማጠናከር በለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡

በተለይም የሚዲያ ባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ በጣቢያዎቹ የሚሰራጩ ይዘቶች የማሕበረሰቡን ችግር ነቅሰው በመለየት መፍትሄ እንዲያመላክቱ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት፡፡

የጀርመን መንግስትም በኢትዮጵያ ለሚዲያ ልማት ዘርፍ መጠናከር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የኦምኒ አትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቤኛ ሲሜሶ በበኩላቸው÷ ወቅታዊ፣ ተዓማኒና የማህበረሰቡን ችግር የሚያነሱ መረጃዎችን ለማሰራጨት በዘርፉ የካበተ ልምድና እውቀት ያላቸው ጋዜጠኞችን ማፍራት ይገባል ብለዋል፡፡

ብቁና የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባርን የተላበሱ የመገናኛ ብዙን ባለሙያዎችን አቅም ለማጠናከር የተለያዩ ሥልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ላለፉት 16 ወራትም በአስተዳደር ፍትህ ሕግ፣ በምርጫ ዘገባ እና የመራጮች ትምህርት፣ በመሰረታዊ የራዲዮ ጋዜጠኝነት፣ በማህበረሰባዊ ዘገባ እና የሚዲያ አዋጭነት እና ዘላቂነት ላይ ሥልጠና መሰጠቱን አመልክተዋል፡፡

ሥልጠናው በሰባት ከተሞች176 ለሚሆኑ ጋዜጠኞች የተሰጠ ሲሆን ÷ ለ164 የራዲዮ ፕሮግራሞች ድጋፍ መደረጉንም አስገንዝበዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!