አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት አካሂደዋል።
የአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ወዳጅነትን የሚያመላክት የዛፍ መትከል መርሐ ግብር፣ የብሔራዊ ሙዚዬም ታሪካዊ ቁሶች እና ምድረግቢ ጉብኝትን ያካተተ ነው፡፡
በተጨማሪም የሁለትዮሽ ውይይቶችና በክሕሎት ልማት እና የካርበን ብድር የመግባቢያ ስምምነቶች ፊርማን አስቀድሞ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫን ያካተተ እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ዋንግ ጉብኝት በሰኔ 2017 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሲንጋፖር ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የተካሄደ ሲሆን÷ ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን ግንኙነት ያሳያል፡፡
ሁለቱ መሪዎች በጉብኝቱ የኢኮኖሚ ትብብርን ለማላቅ፣ ተቋማዊ መስተጋብርን ለማጠናከርና የወል ቅድሚያዎቻቸውን ከፍ አድርጎ ለመከወን መንገዶችን እንደተመለከቱ ተጠቅሷል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!