ስፓርት

ወላይታ ድቻ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል አስመዘገበ

By Abiy Getahun

November 25, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግቦች ውብሸት ክፍሌ እና ቅዱስ ቂርቆስ አስቆጥረዋል፡፡

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ፍቃዱ መኮንን ከመረብ አሳርፏል፡፡

በዚህም ወላይታ ድቻ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል ሲያስመዘግብ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ በውድድር ዓመቱ እስካሁን ምንም ድል ማድረግ አልቻለም፡፡

በሌላ የሊጉ ጨዋታ አዳማ ከተማ ባህርዳር ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የአዳማ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አቡበከር ሳኒ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በተመሳሳይ ስታዲየም የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከነገሌ አርሲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!