አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይና ጉምሩክ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ የኢትዮጵያ እና ቻይናን የጉምሩክ ዘርፍ ትብብር ለማጠናከር ያለመ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብቷል፡፡
ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታን ጨምሮ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገዋል።
በቻይና ጉምሩክ አስተዳደር ሚኒስትር ዴዔታ ዋንግ ጁን የተመራው የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ቆይታው በጉምሩክ ዘርፍ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት እንደሚጎበኝ ተገልጿል፡፡
በወንድሙ አዱኛ