አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምስራቅ እስያ በምትገኘው ታይላንድ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከ13 ሺህ በላይ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።
ይህ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ 18 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ፤ ከ13 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።
በአደጋው ከ2 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተጎጂ መሆናቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል።
በታይላንድ የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው የጎርፍ አደጋ ድንበር ተሻግሮ የታይላንድ አጎራባች ሀገሮች ላይ ጉዳት ማስከተሉም ተነግሯል።
አደጋው እያስከተለ ያለውን ጉዳት ለመቀነስና ለመቆጣጠር ወታደራዊ መርከቦች እና ሄሊኮፕተሮች በማሳተፍ ጭምር የአደጋ መከላከል ስራ እየተሰራ ይገኛል።
በባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በምትገኘው ሃት ያዩ ከተማ በአንድ ቀን ውስጥ 335 ሚሊ ሜትር የተመዘገበ ከባድ ዝናብ በመጣሉ የጎርፍ አደጋ ተከስቷል።
በከተማዋ እንደዚህ አይነት መጠኑ ከፍ ያለ ዝናብ ሲከሰትም ከ300 አመታት በኋላ መሆኑ ተገልጿል።
በተመሳሳይ በቬትናምም በጎርፍ አደጋው ምክንያት የሟቾች ቁጥር በአንድ ሳምንት ውስጥ ወደ 98 ከፍ ብሏል።
በሶስና አለማየሁ