ጤና

ከማርበርግ ቫይረስ ታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው – ዶ/ር መቅደስ

By Yonas Getnet

November 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከማርበርግ ቫይረስ ታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ።

ሚኒስትሯ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ እስካሁን የማርበርግ ቫይረስ ምርመራ ከተደረገላቸው 73 ሰዎች መካከል 11ዱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና አምስቱ ደግሞ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

ከታካሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥም 119 ሰዎች ነጻ መሆናቸው ተረጋግጦ ከማዕከል መውጣታቸውን ጠቁመዋል።

የማርበርግ ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬከተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ በበኩላቸው ፥ የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በየኬላዎች የሚደረገውን ቁጥጥር የማጠናከር፣ የቅኝት ሥራዎችን የማስፋትና ለሕብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ትኩረት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

ማሕበረሰቡ ከጤና ሚኒስቴር የሚሰጡ የጥንቃቄ መመሪያዎችን በመተግበርና ጥቆማዎችን በመስጠት ሃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

በአቤል ነዋይ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!