አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሲዳማ ቡና መቻልን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ቀን 7፡00 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ያሬድ ባየህ በፍጹም ቅጣት ምት እና በጨዋታ 2 ግቦችን ሲያስቆጥር፤ የመቻልን ብቸኛ ግብ ኮሊያን ኮፊ አስቆጥሯል።
የሊጉ 7ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ቀን 10፡00 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሀዋሳ ከተማ እና ፋሲል ከነማን የሚያገናኘው ጨዋታ ይጠበቃል።
እንዲሁም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9፡00 ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሲገናኙ አመሻሽ 12፡00 ሰዓት ላይ ሸገር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!