አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ማጣሪያ ውድድር የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የኬንያ አቻውን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ምድቡን በበላይነት በማጠናቀቅ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀል ችሏል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የኢትዮጵያን ብቸኛ ግብ ዳዊት ካሳው ከመረብ አሳርፏል፡፡