አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) በኳታር ዶሃ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡
ሚኒስትሯ በዶሃ ቆይታቸው ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና መከላከያ ሚኒስትር ሼክ ሳኡድ ቢን አብዱራህማን ቢን ሀሰን አል ታኒ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለጋራ ጥቅም ትብብሮችን ለማሳደግ እንደሚፈልጉ አንስተዋል፡፡
በተለይም በመከላከያ ልዩ ልዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማሳደግና ለማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መምከራቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
በተለያዩ የኢንቨስትመንትና የአቅም ግንባታ መስኮች ትብብራቸውን ለማጠናከር ጽኑ ፍላጎት እንዳላቸውም አመላክተዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ