አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 47ኛው የጉሚ በለል መድረክ “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው፡፡
መድረኩ እየተካሄደ የሚገኘው 20ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ ነው፡፡
የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱራህማን በዚሁ ወቅት፥ ህገ መንግስቱ ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በአብሮነት እንዲኖሩ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል።
አብሮነትን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸው፤ አብሮነት የተረጋጋጠበትና የበለጸገች ሀገር ለመገንባት ሁሉም በጋራ ሊሰራ ይገባል ነው ያሉት፡፡
አለመግባባቶችን በሀገራዊ ምክክሩ መፍታት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለዚህም የምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ በበኩላቸው፥ በሀገረ መንግሥት ግንባታ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ያላቸው ምሁራን አብሮ የመኖር እሴትን ማጎልበት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!