ፋና ስብስብ

አቶ ኩመራ ዋቅጂራ በብዝኃ ህይወት ጥበቃ ላከናወኑት ስራ ተሸላሚ ሆኑ

By Yonas Getnet

November 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጂራ በብዝኃ ህይወት ጥበቃ ላከናወኑት ውጤታማ ስራ የተስክ ኮንዘርቬሽን አዋርድ አሸናፊ ሆነዋል።

አቶ ኩመራ በለንደን በተካሄደው የሽልማት መርሐ ግብር በዘርፉ ከስነ ህይወት ጀማሪ ባለሙያነት እስከ ዋና ዳይሬክተርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የልዑል ዊሊያም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ሽልማቱ በስራ ቆይታቸው ካበረከቱት አስተዋጽኦ በተጨማሪ መንግሥት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት በተመዘገቡ ውጤቶች የተገኘ መሆኑን አቶ ኩመራ ዋቅጂራ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

በአረንጓዴ ዐሻራ እና ሌሎች የብዝኃ ሕይወት ጥበቃ ስራዎች በኢትዮጵያ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸውን እንደ አዋሽ ፓርክ ያሉትን መመለስ እንደተቻለ አመላክተዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች ተሰደው የነበሩ የዱር እንስሳትና አዕዋፋትም በዚሁ ስራ ከመመለስ ባሻገር ቁጥራቸው እየጨመረ መምጣቱን በማሳያነት ጠቅሰዋል።

በዘርፉ ከ30 ዓመታት በላይ ያገለገሉት ዋና ዳይሬክተሩ÷ በተለያዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርኮች የላቀ አበርክቶ ያላቸውን የምርምር ስራዎች አከናውነዋል።

የባሌ ብርቅዬ ጦጣ በፓርኩ መኖሯን ካረጋገጡና በዓለም አቀፍ ቅርስነት ካስመዘገቡ ተመራማሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ኩመራ÷ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ዝሆን መኖሩን የሚያረጋግጠውን የጥናት ቡድንም በስፍራው መርተዋል።

በተጨማሪም የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በመስራት ከኢትዮጵያ ውጭ በተለያዩ ሀገራት ትምህርቶችንና ስልጠናዎችን ተከታትለዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!