አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 12ኛው ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት መርሐ ግብር በመጪው ቅዳሜ ይካሄዳል፡፡
የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት በየዓመቱ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር መለኪያ መስፈርት በማወዳደር ዕውቅና እና ሽልማት ይሰጣል።
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቴዎድሮስ መብራት የዘንድሮውን ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ሥነ ሥርዓት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷ በውድድሩ ከተመዘገቡት 65 ድርጅቶች ውስጥ 63 ድርጅቶችና ተቋማት እስከ መጨረሻ ደርሰዋል፡፡
ከተመዘገቡ ተቋማትና ድርጅቶች 34 በአምራች ዘርፍ፣ 12 ለትርፍ የተቋቋሙ አገልግሎት ሰጪዎች፣ 10 በጤና ዘርፍ፣ 5 በአገልግሎት ዘርፍ፣ 3 በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ እና 1 በኮንስትራክሽን ዘርፍ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ በታላቁ ቤተ መንግሥት እንደሚካሄድ ጠቅሰው÷ ውድድሩ 7 የአሰራር ሥርዓት መስፈርቶች እንዳሉት ተናግረዋል።
በ2000 ዓ.ም የተቋቋመው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ለጥራት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ የሽልማት ሥርዓት በመዘርጋት የሀገሪቱን ዓለም አቀፍ የተወዳዳሪነት ብቃት በማሳደግ ጥራት የሀገሪቱ ባህል እንዲሆን ማድረግን ያለመ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
በአንዷለም ተስፋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!