አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማያቋርጥ መፍጠር እና መፍጠን መርህ እየሰራን የኢትዮጵያን ብልፅግና እናረጋግጣለን አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
በአዲስ አበባ ከተማ ‘በመደመር መንግሥት እይታ የዘርፎች እመርታ’ በሚል መሪ ሐሳብ ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ባለፉት ቀናት ሲሰጥ የነበረው 2ኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቅቋል።
ከንቲባዋ በማጠቃለያው ላይ እንዳሉት፤ አመራሩ በሁሉም መስኮች በስልጠናው ያገኘው ግንዛቤ በተጨባጭ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት እና የተገኙ አበረታች ውጤቶችን የመስክ ምልከታም አካሂዷል።
በሁሉም መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠልና ተግዳሮቶችን ወደ ድል በመቀየር፣ የተሻለችና የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት ትኩረት እንዲደረግባቸው አስገንዝበዋል።
በለየናቸው የትኩረት ዘርፎች የግብርና እና ገጠር ትራንስፎርሜሽን፣ የኢንዱስትሪ እንዲሁም የቱሪዝምና ከተማ ልማት ዘርፎች እመርታን ለማስመዝገብ መግባባት ፈጥረናልም ነው ያሉት።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!