ጤና

በአንድ ጀምበር 4 ሺህ ዩኒት ደም የማሰባሰብ ዘመቻ ሊጀመር ነው

By Adimasu Aragawu

November 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) “ቢግ ብሊዲንግ” የተሰኘ በአንድ ጀምበር 4 ሺህ ዩኒት ደም የማሰባሰብ ዘመቻ በመጪው ቅዳሜ ይጀመራል አለ የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት፡፡

አገልግሎቱ ይህንን የገለጸው በሞጆ ከተማ ከደም ባንኮች እና የክልል የደም ባንክ ተወካዮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ጋር በደምና ደም ተዋጽኦ ጥራትና ደህንነት ዙሪያ በተወያየበት ወቅት ነው፡፡

የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጤናዬ ደምሴ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የዘመቻ ስራውን ለማድረግ የዝግጅት ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

“ቢግ ብሊዲንግ” የተሰኘው ዘመቻ በአፍሪካ ደረጃ ሊዘጋጅ መታሰቡንና በዘመቻው ከሚሳተፉ ሀገራት ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ገልጸው÷ እንደ አፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ዩኒት ደም ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

ዘመቻው በርካታ የደም ክምችት ከማግኘት ባለፈ በአፍሪካ ሀገራት መካከል አንድነትና ትስስርን ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሁሉም ደም መለገስ የሚችል ዜጋ እንዲሁም በጎ አድራጊ ማሕበራትና ግለሰቦች በዘመቻው በመሳተፍና ቀጣይነት ያለውን ድጋፍ በማድረግ ህይወትን እንዲያስቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአመለወርቅ ደምሰው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!