የሀገር ውስጥ ዜና

የደን ሃብት ልማትን ይበልጥ ለማጠናከር የዘርፉ እውቀት ማዕከላት ሚና…

By Yonas Getnet

November 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የደን ሃብትን ወደ ነበረበት ለመመለስ የጀመረቻቸው ተስፋ ሰጭ ጥረቶች ዓለም አቀፍ እውቅና እየተቸራቸው ነው አሉ ምሁራን።

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ መምህር ጸጋይ በቀለ (ፕ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት ÷የደን ሃብት ከተፈጥሮ ጸጋነት ባሻገር የሕልውና ጉዳይ በመሆኑ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው።

ኢትዮጵያም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የደን ሃብትን ለማልማት ባለፉት ዓመታት የሰጠችው ትኩረት የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

የኮሌጁ ዲን ሃብታሙ ወ/አማኑኤል (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ የደን ሃብትን በአግባቡ ለመጠበቅ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ቀጣይነትን ባረጋገጠ መልኩ መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

የደን ልማት ተጠቃሚነትን ይበልጥ ለማጠናከርም የደን ሃብት እውቀት ማዕከላትን ማስፋፋት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

ከዚህ አንጻር በኮሌጁ እየተሰሩ ላሉ ተግባራት ተጨማሪ አቅም የሚሆን የደን ጥናት ማዕከል ከፌዴራል ተቋማት ጋራ በቅንጅት ወደ ሥራ መግባቱን ምሁራኑ ተናግረዋል።

የማዕከላቱ መስፋፋት ሀገሪቱ በደን ሃብት ዘርፍ ያላትን አቅም በአግባቡ መረዳት የሚያስችሉና ለምርምር እንዲሁም እንደግብዓት የሚውሉ መረጃዎችን ለማደራጀት ያግዛል፡፡

የደን ጥበቃን ለማጠናከር እና የመፍትሄ ርምጃዎችን ለመውሰድ የተደራጁ የእውቀት ማዕከላት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በነገዎ ብዙነህ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!