አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጥራት ያለው የጤና መድህን አገልግሎት ተደራሽነትን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት፡፡
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ወርቁ እንዳሉት÷ ጤና መድህን የመክፈል አቅም የሌላቸው ዜጎች አስፈላጊውን የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡
ዜጎች የጤና መታወክ ሲገጥማቸው ያለ ተጨማሪ ሕክምና ወጪ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ያለ ምንም ስጋት እንዲታከሙ የሚያስችል መሆኑን ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡
የጤና መድህን አገልግሎት አሁን ላይ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በ1 ሺህ 195 ወረዳዎች እየተተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በዚህም 13 ነጥብ 67 ሚሊየን አባወራ/እማወራ አባላትን ማፍራት የተቻለ ሲሆን ÷ ከ63 ሚሊየን በላይ ዜጎችም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
በቀጣይ የጤና መድህን አገልግሎት ያልተጀመረባቸውን ወረዳዎች ተደራሽ ለማድረግ በቅንጅት እንደሚሰራ ነው የገለጹት፡፡
ከባለፈው ጥቅምት ጀምሮ እስከ የካቲት ወር ድረስም የማሕበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የንቅናቄ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
አባላት የገቢያቸውን መጠን መሰረት ባደረገ መልኩ ፍትሃዊ መዋጮ እንዲከፍሉ ለማድረግ አሰራር እየተዘረጋ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡
የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የፋይዳ መታወቂያ አስፈላጊ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!