አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል የሚገኘውን የሸበሌ ሪዞርት ግንባታ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቀ በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡
የገበታ ለትውልድ የቱሪዝም ሥራዎች አካል የሆነው የሸበሌ ሪዞርት ፕሮጀክት የመጨረሻ ግንባታ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።
በመድረኩ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ዑስማን እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም የሸበሌ ሪዞርት ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ሥራ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
የሸበሌ ሪዞርት ፕሮጀክት ግንባታን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡
ፕሮጀክቱን ለማስመረቅ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር መደረጉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
ከጅግጅጋ 29 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በፋፈን ዞን የሚገኘው ሸበሌ ሪዞርት በ385 ሄክታር መሬት ላይ ነው ያረፈው፡፡
ሪዞርቱ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ለክልሉና ለአከባቢው ከፍተኛ የቱሪስት መዳረሻ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!