አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ደረጃ 20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በቡሌ ሆራ እየተከበረ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰዓዳ አብዱራህማን፣ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በዓሉ የክልሉን ሕዝብ ባህል፣ ማንነትና ትውፊት በሚያንጸባርቅ መልኩ ነው በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው፡፡
በትናንትናው ዕለት በኦሮሚያ ክልል 20ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አስመልክቶ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡
20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ ከፊታችን ሕዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይከበራል፡፡
በመራኦል ከድር