አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ለብዝሃ ማንነታችን እውቅና የሰጠ ነው አሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር።
በኦሮሚያ ክልል ደረጃ 20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በቡሌ ሆራ እየተከበረ ይገኛል፡፡
አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት ተከብሯል፤ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት እየተጠናከረ መጥቷል።
በዓሉ የክልሎቹ ልማት እንዲስፋፋ፣ የቱሪዝም ሃብቶቻቸው እንዲተዋወቅ፣ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲገለጡ እንዲሁም ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁና ሌሎችም እንዲጀመሩ አስተዋጽኦ እንደነበረው ጠቅሰዋል።
በዓሉ ለብዝሃ ማንነታችን እውቅና የሰጠ ነው ያሉት አፈ ጉባዔው÷ የዘንድሮ በዓል ኢትዮጵያ እየመከረች በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ በደረሰችበት ወቅት የሚከበር በመሆኑ የተለየ እንደሆነ ተናግረዋል።
እንዲሁም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበት እንዲሁም የሀገራችን የተስፋ ብርሃን መታየት በጀመረበት ወቅት የሚከበር መሆኑ ለየት ያደርገዋል ብለዋል።
በዓሉ የጋራ ታሪክ፣ ባህልና እሴቶቻችን የምናሳይበት እንዲሁም የኑሮ መስተጋብራችንን የምናበለጽግበት እና ለመላው ዓለም የምናስተዋውቅበት መድረክ ነው ሲሉም አመላክተዋል።
የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰዓዳ አብዱራህማን በበኩላቸው÷ በዓሉ የኢትዮጵያ ህዝቦች በአንድነት ባህልና እሴታቸውን የሚያሳዩበት ብሎም ቃልኪዳናቸውን የሚያድሱበት መሆኑን ገልጸዋል።
በዓሉ በክልሉ በየደረጃው ሕዝብን ባሳተፈ መልኩ በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች ሲከበር መቆየቱን አንስተዋል።
የሐሳብና የግጭት አዙሪትን ለመፍታት በባህልና እሴታችን መሰረት በውይይትና በምክክር መፍታት አለብን በማለት ገልጸው÷ ለዚህም በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማካኝነት ውይይቶች እየተደረጉ መሆናቸውን አመላክተዋል።
በመራኦል ከድር
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!