የሀገር ውስጥ ዜና

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ለጎንደር ከተማ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

By sosina alemayehu

December 01, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ለጎንደር ከተማ አስተዳደር የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ጽ/ቤቱ ለሁለት ት/ቤቶች ለሚኒ ሚዲያ አገልግሎት የሚውል ግብዓት እና የተለያዩ የስፖርት ትጥቆችን ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡

በተጨማሪም ድጋፉ 16 ሚሊየን ብር የሚያወጡ 20 የአካል ጉዳተኛ ዊልቸሮችን ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ ቻላቸው ዳኛው እንዳሉት÷ የተደረገው ድጋፍ በት/ቤቶች እና በስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን የግብዓት እጥረት የሚያቃልል ነው፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ላደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በበላይነህ ዘላለለም