እንኳን ደስ አለን!
ይህ እግር ኳስ ወዳድ ለሆነው ህዝባችን ትልቅ የድል ብስራት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን (ቀይ ቀበሮዎቹ) ኬንያን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ከ22 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፋቸው እንኳን ደስ አለን።
በስፖርቱ ዘርፍ ታዳጊዎች ላይ በርትተን ከሰራን እግር ኳሳችን በአህጉራዊና በዓለም አቀፋዊ መድረኮች ከፍ የሚልበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ይህ ስኬት አመላካች ነው፡፡
የዛሬው ውጤት እንዲገኝ ሚናችሁን ለተወጣችሁ አካላት ሁሉ ምስጋናዬን እያቀረብሁ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!