ስፓርት

ቅዱስ ጊዮርጊስ አርባምንጭ ከተማን አሸነፈ

By Adimasu Aragawu

December 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ8ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ፀጋ ከድር አስቆጥሯል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ ከሁለት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ ድል ተመልሷል፡፡

በሌላ የሊጉ ጨዋታ መቻል እና ድሬዳዋ ከተማ 1 አቻ በሆነ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቅቀዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ለድሬዳዋ ከተማ መሐመድኑር ናስር ሲያስቆጥር የመቻልን ግብ አብዱልከሪም ወርቁ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በጨዋታው 30ኛው ደቂቃ ላይ የመቻል አማካይ መናፍ ኢሞሮ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበት 50ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ የድሬዳዋው አማካይ አቡበከር ሻሚል በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል፡፡

የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ነገሌ አርሲ ከሸገር ከተማ ይገናኛሉ፡፡