የሀገር ውስጥ ዜና

በደሴ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Adimasu Aragawu

December 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ደሴ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በከተማዋ ሰኞ ገበያ ክፍለ ከተማ ቢለን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን በደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ፈቲያ ሀሰን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

አደጋው በዛሬው ዕለት ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ የደረሰ መሆኑን ነው የገለጹት።

አደጋው የጭነት ተሽከርካሪ መኪና በመገልበጡ ምክንያት መከሰቱን አንስተው÷ የ3 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት እንደደረሰ አስረድተዋል።

በአደጋው በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የገለጹት ኃላፊዋ÷ የተሽከርካሪው ሹፌር በህግ ስር ሆኖ ህክምና እየተከታተለ መሆኑን አውስተው÷ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን አመላክተዋል።

በከድር መሀመድ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!