የሀገር ውስጥ ዜና

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል

By Yonas Getnet

December 03, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 20ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በድምቀት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል አለ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ።

የዘንድሮው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ-ብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ተመስገን ካሳ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፥ በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከአጎራባች ክልሎች ጋር በመተባበር የቅድመ ዝግጅት ስራ ተሰርቷል፡፡

ዕለቱ ክልሉን ይበልጥ ለማስተዋወቅ የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፥ እንግዶች ወደ በዓሉ መጥተው እስከሚመለሱ ድረስ ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።

በሰለሞን በየነ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporationFacebook www.facebook.com/fanabroadcastingFacebook https://web.facebook.com/fanasportFacebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporateTelegram t.me/fanatelevisionWebsite www.fanamc.comTikTok www.tiktok.com/@fana_televisionWhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainmentTikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainmentAmharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!