አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ÷ ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ጋር እ.ኤ.አ በ2027 አፍሪካን በሚገባ የሚወክል ኮፕ32 በማዘጋጀት ረገድ በጋራ ስለምንሰራባቸው መንገዶች ተወያይተናል ብለዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ብሎም ዋና ፀሐፊው ከቡድናቸው ጋር በመሆን ኮፕ32 ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ እተማመናለሁ ሲሉም ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!