የሀገር ውስጥ ዜና

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የብልፅግና ተምሳሌት ነው – አቶ ጥላሁን ከበደ

By Yonas Getnet

December 04, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን የሰላም፣ የመቻቻል እና የብልፅግና ተምሳሌት ነው አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ።

‘ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት’ በሚል መሪ ሀሳብ 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል በክልል ደረጃ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ተከብሯል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት፤ የማንሰራራት ዘመን ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ በርካታ ለውጦች ታይተዋል።

የበዓሉ መከበር ክልሉን የሰላምና የመቻቻል እንዲሁም የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በጋራ ለመስራታችን ማሳያ ነው ብለዋል።

የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አዳማ ትንፋዬ በበኩላቸው፤ ክልሉን ከ32 በላይ ብሔረሰቦች ተጣምረው መስርተውታል ብለዋል።

የክልሉ ብሔረሰቦች ከአብሮነትና ከመቻቻል የሚለያቸው ምንም ኃይል የለም ሲሉም ገልጸዋል።

የዘንድሮ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል ኢትዮጵያ በለውጥ ጎዳና ላይ እየተጓዘች ባለችበትና በርካታ ስኬቶችን ባስመዘገበችበት ወቅት መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የብሔረሰቦች ቀን መከበር ለአንድነትና ለጋራ ተግባራት መጠናከር የጎላ ፋይዳ እንዳለው ተመላክቷል።

በታሪክነሽ ሴታ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!