የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሉ ከ21 ሺህ 680 ካሬ ሜትር በላይ የከተማ መሬት ከምዝበራ ማዳን ተቻለ

By Adimasu Aragawu

December 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥነ ምግባር እና ፀረሙስና ኮሚሸን ከ21 ሺህ 680 ካሬ ሜትር በላይ የከተማ መሬት ከምዝበራ ማዳን ተችሏል አለ።

“ትውልድን በሥነ ምግባር ፤ ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ሐሳብ በክልሉ የተከበረው 22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ማጠቃለያ መርሐ ግብር በወላይታ ሶዶ ተካሂዷል።

የኮሚሸኑ ኮሚሸነር ተካልኝ ጋሎ በዚህ ወቅት÷ ሙስናና ብልሹ አሰራር የሀገሪቱን እድገት የሚያቀጭጭ መሆኑን ገልጸዋል።

ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የሙስና ድርጊትን መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማጠናከር ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በክልሉ የ3 ሺህ 500 አመራሮች እና 29 ሺህ ባለሙያዎች ሀብት መመዝገቡን አንስተዋል።

በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የህዝብና መንግሥት ሀብት ከምዝበራ ማትረፍ መቻሉን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ሁለት የመንግሥት ቤቶችና 21 ሺህ 680 በላይ ካሬሜትር የከተማ መሬት ከምዝበራ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል።

በማቴዎስ ፈለቀ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!