የሀገር ውስጥ ዜና

ኢዜማ የሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎቹን ለኮሚሽኑ አስረከበ

By Adimasu Aragawu

December 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) የሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎቹን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክቧል።

አጀንዳዎቹን የፓርቲው መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና ሌሎች አመራሮች ለኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች አስረክበዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት÷ ኮሚሽኑ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ አጀንዳዎችን መረከቡን አውስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ኮሚሽኑ ሲቋቋም ጀምሮ ሂደቱን እየደገፈ መሆኑን አንስተዋል።

ፓርቲው የተደራጀ አጀንዳ በማስረከቡ በኮሚሽኑ ስም ያመሰገኑት ዋና ኮሚሽነሩ÷ አጀንዳዎቹ ለሀገራዊ ጉባኤው ጥቅም ላይ ይውላሉ ብለዋል።

የምክክር ሂደቱን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ዋና ኮሚሽነሩ÷ ሂደቱ እንዲሳካ የፓርቲዎች ትብብር በቀጣይ ጊዜያትም እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

የኢዜማ መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በበኩላቸው ሀገራዊ ምክክሩ የሀገራችንን መሠረታዊ ችግሮች ለመፍታት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢዜማ ኮሚሽኑ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለማገዝ ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡

ኢዜማ በሁለት ከተማ አስተዳደሮችና በ11 ክልሎች በተደረጉ የምክክር ምዕራፎች በስፋት መሳተፉ በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!