አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ የሚታወቁ የአፍሪካ የቀድሞ መሪዎች ልጆች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ የፓትሪስ ሉሙምባ ልጅ፣ የኒልሰን ማንዴላ የልጅ ልጅ፣ የኳሜ ኑኩሩማ ልጅ፣ የጁልየስ ኔሬሬ ልጅ፣ የኬኔት ካውንዳ ልጅ እና ሌሎችም የአፍሪካ ሕብረት መስራችና የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ ጅማሮ ተሳታፊዎች ቤተሰቦች ተሳትፈዋል።
ጎብኚዎቹ ለአፍሪካ ሰላምና ልማት በፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ የሚታወቁ ሲሆኑ÷ በምልከታቸው ኢትዮጵያ በራስ አቅም ይህንን መስራቷ የፈጠረባቸውን መደነቅ አጋርተዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በአካል ተገኝተው ሲመለከቱት ከጠበቁት በላይ ሆኖ እንዳገኙትም ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት ላይ ለመታደም ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ጎብኚዎቹ÷ ወደ በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸው ይታወሳል።
በመዲናዋ በነበራቸው ጉብኝት ወቅትም ኢትዮጵያ ለፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ መስፋፋት የነበራትን ሚና እና ያልተቋረጠ ተጋድሎ የሚያሳዩ ስራዎችን ተመልክተዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!