የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ይበጃሉ ያላቸውን አጀንዳዎች የልየታ ስራ እያጠናቀቀ ነው – መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)

By Adimasu Aragawu

December 09, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ የቆዩ ችግሮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ይበጃሉ ያላቸው አጀንዳዎች የልየታ ስራ እየተጠናቀቀ ነው አሉ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)።

ኮሚሽኑ በእስካሁን ሂደት የተከናወኑ ተግባራትንና የተገኙ ውጤቶችን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ገለጻ እያደረገ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች፣ አምባሳደሮች፣ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት÷ ሀገራዊ ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋትና ዴሞክራሲን ለማስፈን በምክክር ላይ የተመሰረተ መፍትሔ ለማምጣት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ለዚህም ኮሚሽኑ የሁሉም ድምጽ የሚሰማበት አካታችና አሳታፊ ሂደትን እየተከተለ እንደሚገኝ ገልጸው÷ ነጻ፣ ገለልተኛና ተዓማኒነት ያላቸው አሰራሮችን በመከተል ሥራውን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በሂደቱም አሳታፊ በሆነ መንገድ በኢትዮጵያ በቆዩ ችግሮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ይበጃሉ የተባሉ አጀንዳዎች ልየታ ስራን እያጠናቀቀ መሆኑን አስረድተዋል።

የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ስራው ውጤታማ እንዲሆን መስራት ሌላው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን መግለፃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!