ስፓርት

የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ክስ ቀረበባቸው

By Adimasu Aragawu

December 09, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማሕበር (ፊፋ) ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

የፊፋው ፕሬዚዳንት ክስ የቀረባበቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሸነፉት የፊፋ የሰላም ሽልማት ስለመሆኑ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የሰላም ሽልማቱን ሲያዘጋጁ የተቋሙን ኮሚቴ እንዲሁም ምክትል ፕሬዚዳንቱን አለማማከራቸው የተገለጸ ሲሆን÷ የፊፋን የፖለቲካ ገለልተኝነት በተደጋጋሚ መጣሳቸው ተመላክቷል፡፡

የሥነ ምግባር ኮሚቴው የፊፋ የሰላም ሽልማትን ለማስተዋወቅና ለመሸለም በተደረገው ውሳኔ ዙሪያ ከፊፋ የሥርዓት ህጎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን እንዲመረምር ጠይቋል።

ትራምፕ የሰላም ሽልማትን የተቀበሉት ባሳለፍነው አርብ በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የፊፋ 2026 የዓለም ዋንጫ የዕጣ ድልድል ማውጣት ሥነ ሥርዓት ላይ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

በወቅቱም ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋንጫ፣ ሜዳሊያ እና የምስክር ወረቀት ማበርከታቸው ይታወሳል፡፡

ፊፋ የሰላም ሽልማቱን ያዘጋጀው ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በወንድማገኝ ፀጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!