አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በከተማዋ የተዘጋጀውን የኤምባሲዎች ውድድር አሸንፏል፡፡
በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ የዓለም ሀገራት ኤምባሲዎች የተሳተፉበት የአሜሪካ ንግድ ማዕከል ያዘጋጀው የዐውደ ርዕይና ባዛር መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና አፈላል ሥርዓት፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ውዝዋዜዎች፣ የአክሱም ሐውልት፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ ጥንታዊቷ የሐረር ከተማ፣ የሰሜን እና ባሌ ተራሮችን ጨምሮ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ሃብቶች ቀርበዋል፡፡
በዚህም በዕለቱ ዳኞች ምርጫ 70 ኤምባሲዎችን በመብለጥ በአሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዓመቱ ምርጥ ኤምባሲ ተብሎ ተመርጧል፡፡
በዐውደ ርዕይ እና ባዛሩ ላይ ከ8 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን ቡና በመቅመስ በርካታ አሜሪካውያን፣ የዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪዎችና ጎብኚዎች መሳተፋቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ያሉ ኢንቨስትመንት ዕድሎች፣ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶችና የቱሪዝም መስሕቦችን የሚያሳይ ቪዲዮ ለእይታ ቀርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ባህላዊ ውዝዋዜ ትርዒት፣ ባህላዊ ምግብና መጠጦች፣ ባህላዊ የቡና አፈላል ሥነ ሥርዓት የዝግጅቱ አካል እንደነበር ኤምባሲው ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል፡፡
ዝግጅቱን ለመጎብኘት የመጡ እንግዶች የኢትዮጵያን የቱሪዝም መስሕቦችን ለመጎብኘት በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ፍላጎት አሳይተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!