ዓለምአቀፋዊ ዜና

አሜሪካና ጃፓን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አደረጉ

By Adimasu Aragawu

December 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ኒውክሌር የመሸከም አቅም ያላቸው ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች እና የጃፓን ተዋጊ ጄቶች የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አድርገዋል፡፡

ሀገራቱ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ያደረጉት በቅርቡ ቻይና እና ሩሲያ ተመሳሳይ ልምምድ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ሁለት የዩኤስ ቢ-52 ስትራቴጂካዊ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ከሦስት የጃፓን ኤፍ-35 ስውር ተዋጊዎች እና ሶስት ኤፍ-15 የአየር ጄቶች ጋር ሲበሩ መታየታቸው ተመላክቷል፡፡

የጃፓን መከላከያ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባስተላለፈው መልዕክት ÷ ሁለቱ ሀገራት የማንኛውንም ኃይል ሙከራ ለመከላከል በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ቻይና በበኩሏ÷ የጃፓን ተዋጊ ጄቶች እንቅስቃሴ ከጃፓን በስተደቡብ በኩል ያለውን የአየር ክልል አደጋ ላይ እየጣሉት ይገኛሉ ስትል ወንጅላለች።

ዋሽንግተን የቻይናን ድርጊት ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት አይጠቅምም ያለች ሲሆን ÷ ከጃፓን ጋር ያላት ጥምረት እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥታለች፡፡

የጃፓን የጦር ኃይል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሂሮአኪ ኡቺኩራ ቻይና እና ሩሲያ በጋራ ወታደራዊ ልምምድ በጃፓን ላይ ያነጣጠረ የኃይል ርምጃ በግልፅ እያሳዩ ነው ማለታቸውን ዘ ኢንዲፐንደንት ዘግቧል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉኦ ጂያኩን ከሩሲያ ጋር ያደረጉት ልምምድ የሁለቱ ሀገራት ዓመታዊ የትብብር እቅድ አካል መሆኑን ገልጸው ÷ የቀጣናውን ሰላምና መረጋጋት ለመጠበቅ ቁርጠኛ መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook WMCC Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!