አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአንጎላ ሉዋንዳ እየተካሄደ በሚገኘው 4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ በሴቶች የ3 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ አሸንፋለች፡፡
በርቀቱ ኤልሳቤት አማረ 1ኛ በመሆን ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ ያስገኘች ሲሆን፥ ኬንያና ዩጋንዳ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡
በተጨማሪም በ1500 ሜትር የወንዶች ውድድር የብር ሜዳልያ አግኝታለች፡፡