አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በለተለዩ ዘርፎች በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ ነው አሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፡፡
በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ “የጉባ ብስራቶች ፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሃሳብ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ አቶ አወል አርባ፣ የሲዳማ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ በየነ በራሳ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ሀገር የሚገነባው የሕዝብን ተጠቃሚነት በሚያረጋገጥ የለውጥ አስተሳሰብ ነው።
የስንዴ ምርት፣ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ፣ የአረንጓዴ ዐሻራ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት ማስመዘገብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የከተማ ኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ እየቀየረ እንደሚገኝ ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡
በጉባ ላይ የታየውን የልማት አንድነት በተለያዩ ዘርፎች ላይ መድገም እንደሚገባ ጠቁመው ÷ ለዚህም ሁሉም በትብብር ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
ሀዋሳ ከተማ የብልጽግና ተምሳሌትና የተሞክሮ ማዕከል እንድትሆን ይበልጥ መስራት አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
አቶ በየነ በራሳ በበኩላቸው÷ ሀዋሳ ከተማን ውብና ምቹ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
ከተማን በአንድ አካል ብቻ መቀየር የማይቻል በመሆኑ በመደመርና ሕዝባዊ ቅንጅትን በማስተባበር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
በፍቅርተ ከበደ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!