አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገርን ወደ ከፍታ ለማሸጋገር ከሕዝብ ጋር በቅንጅት መስራት ወሳኝ ነው ነው አሉ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፡፡
በአማራ ክልል ደሴ ከተማ “የጉባ ብስራቶች ፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሃሳብ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በዚህ ወቅት÷ መንግሥት በሕዝቡ ዘንድ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
በተለይም በተለያዩ አካባቢዎች ሥር ሰደው የቆዩ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የሚገጥሙ ችግሮችን ወደ እድል እየቀየርን ሀገርን ወደ ከፍታ ማሸጋገር ይገባናል ያሉ ሲሆን÷ ለዚህም ከሕዝብ ጋር በቅንጅት መስራት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
መንግሥት የማሕበረሰቡን ጥያቄ ለማድመጥና ችግሮችን ለመፍታት በየአካባቢው የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱን ያነሱት ሚኒስትሯ÷ በደሴ ከተማም የማሕበረሰቡን ሃሳብ በማድመጥ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚሰራ አመልክተዋል።
ከአሁን ቀደም በክልሉ የልማት ጥያቄዎች አለመፈታት እንደሚስተዋልና አሁን ላይ ግን ከመሰረቱ መልስ ለማግኘት በተግባር የተረጋገጠበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ያሉት ደግሞ የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ናቸው።
በዚህም በደሴ ከተማ በተከናወኑ በርካታ ሥራዎች ይነሱ የነበሩ የመሰረተ ልማትና የማሕበራዊ ጉዳይ ጥያቄዎች መልስ ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ ነዋሪዎች በበኩላቸው÷ ተግዳሮት የነበሩና በይደር ሲንከባለሉ የቆዩ የልማት ጥያቄዎች ከለውጡ ወዲህ በመጣ ሥር ነቀል ለውጥ መፍትሔ እየተሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የዘመናት ጥያቄያቸው ተፈትቶ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልጸው÷ ብልጽግና የማይደፈሩ የሚመስሉ የልማት መሰረቶችን በደሴ ከተማ ላይ ተክሏል ሲሉ በአጽንኦት አንስተዋል፡፡
በአመለወርቅ መኳንንት እና ከድር መሃመድ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!