አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሕዝብ የሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ለማስቻል መንግሥት በቁርጠኛነት ይሰራል አሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ።
“የጉባ ብስራቶች ፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሃሳብ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በተገኙበት በሆሳዕና ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።
ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ እየመጣ ያለው ለውጥ የክልሉ መንግሥት እና ማህበረሰቡ ተደማምጠው እየሰሩ ስለመሆናቸው ማሳያ ነው።
ከክልሉ ሕዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ለማስቻል መንግሥት በቁርጠኛነት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
እናትዓለም መለሰ በበኩላቸው፤ ማህበረሰቡ የነበረውን ትብብር በማጠናከር በሚያጋጥመው ችግር ላይ በጋራ በመሥራት የመፍትሔ አካል ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ከዚህ በፊት በተከታታይ በተደረጉ ውይይቶች የተነሱ ጥያቄዎች እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተቀረፉ እንደሚገኙ የገለጹት ደግሞ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማና ኢንዱስትሪ ልማት ክላስተር አስተባባሪ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል ናቸው።
በውይይት መድረኩ የተነሱ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ እና በፍጥነት ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።
በውይይቱ የተሳተፋ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች መንግሥት እየሰራቸው የሚገኙ ሁሉን አቀፍ የልማት ሥራዎች የክልሉን ማህበረሰብ እኩል ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይም የንፁህ መጠጥ ውሃና መብራት፣ የመንገድ ግንባታ፣ የአውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ የወጣቶች የሥራ ዕድል፣ የአካባቢውን ሀብት ለይቶ ማልማት እና በሌሎች ዘርፎች ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባን ብለዋል።
በቅድስት አባተ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!