የሀገር ውስጥ ዜና

ሕዝቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች መንግሥት በተግባር ይመልሳል – ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)

By Yonas Getnet

December 13, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕዝቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች መንግሥት በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር ይመልሳል አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)።

“የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሃሳብ ከሻሸመኔ ከተማ እና ምዕራብ አርሲ ዞን ነዋሪች ጋር ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።

ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መንግሥት ሕዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በጊዜው ለመመለስ ተግቶ ይሰራል።

በክልል፣ በከተማ እና በቀበሌ ደረጃ ሊመለሱ ለሚችሉ ጥያቄዎች ተገቢ የሆነ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት እንደሚገባ ገልጸው÷ የፌዴራል መንግሥትን ቀጥተኛ ተግባርና እገዛ የሚሹት ጥያቄዎችን ደግሞ የቤት ስራ ወስደን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር እንመልሳለን ብለዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ መንግሥቱ በቀለ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሕዝቡ ያነሳቸው ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ የሚመለሱ እንዲሁም የክልል መንግሥት በውሳኔና በእቅድ የሚመልሳቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሕዝብና መንግሥት በትብብር ሲሰራ ሀገርን መለወጥ እንደሚቻል ሻሸመኔ ማሳያ እንደሆነችና ሕዝቡ የባሕር በር ጥያቄን እየደገፈ እንደሚገኝ የገለጹት ደግሞ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ ናቸው።

በውይይቱ የተሳተፉ የማሕበረሰብ ክፍሎች የሕዝብ ጥያቄን የሚሰማ መንግሥት በመፈጠሩ ደስታቸውን በመግለጽ÷ ከንግግር ያለፉ በተግባር የተገለጡ ልማቶች እያሳየን በመሆኑ ተግባሩን በሙሉ ልባችን እንደግፋለን ብለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃም የኢትዮጵያ ከፍታ የሚጨምሩ እንደ ጋዝ ምርትና የማዳበሪያ ፋብሪካ ያሉት ሀገራችን ትልቅነት የሚያፋጥኑ ናቸው በማለት ገልጸው÷ በተለይም የባሕር በርን ለማሳካት መንግሥት የጀመረው ድፍረት የተሞላበትና በእውቀት የተመራ አካሄድን እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል።

ለረጅም ዓመታት የሕዝብ ጥያቄ ሆኖ የቀጠለው የመጠጥ ውሃ ችግር፣ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች፣ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ችግሮች መንግሥት ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥም ጠይቀዋል።

በጥላሁን ይልማ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast  YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!