የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ፈተና ውስጥ ሆና ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች ከብልጽግና ጉዞዋ የሚያስቀራት እንደሌለ ማሳያ ነው – አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

By Adimasu Aragawu

December 13, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በፈተና ውስጥ ሆና ያስመዘገበቻቸው ሁሉን አቀፍ ስኬቶች ከጀመረችው የብልጽግና ጉዞ የሚያስቀራት ኃይል እንደሌለ ማሳያ ነው አሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲኦ ዞን ዲላ ከተማ “የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ሃሳብ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በታላቅ ፈተና ውስጥ ሆና በርካታ ስኬቶችን ተቀዳጅታለች።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የገጠሙት ችግሮችን በመፍታት የዘመናት የሕዝብን ቁጭት ወደ ሐሴት መቀየር መቻሉን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ በስንዴ ምርት በተሰራው ስራ ከራስ አልፎ ለውጪ ገበያ ማቅረብ መቻሉን ገልጸው÷ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች በተሰራው ስራ የሀገሪቱን እምቅ የቱሪዝም አቅም ማነቃቃት ተችሏልም ነው ያሉት።

ለዘመናት ያልተጠቀምንባቸውን ነዳጅን ጨምሮ ከፍተኛ የማዕድን ሃብቶቻችንን በአግባቡ መጠቀም ጀምረናል ያሉት ሚኒስትሩ÷ በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በከተማና የገጠር ኮሪደር ልማት ዓለም አቀፍ እውቅናን ያተረፉ ስራዎችን ማሳካት ተችሏል ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ሚኒስትሩን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተገኝተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!