የሀገር ውስጥ ዜና

የባሕር ዳር ‎የኮሪደር ልማት ከጣና ኃይቅ ዳርቻ ጋር ተሳስሮ መልማቱ ለከተማዋ ውበት…

By Adimasu Aragawu

December 13, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎የባሕር ዳር የኮሪደር ልማት ከጣና ኃይቅ ዳርቻ ጋር ተሳስሮ እንዲለማ መደረጉ የከተማዋ ውበት ይበልጥ እንዲገለጥ አስችሏል አሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር)፣ ‎የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች የባሕር ዳር የልማት እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል።

ከጎበኟቸው የልማት ስራዎች መካከል የኮሪደር ልማት፣ የአረንጓዴ መናፈሻ፣ የመንገድ፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትና የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ይገኙበታል።

‎ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳልት÷ ደረጃቸውን ጠብቀው እየተገነቡ የሚገኙ የኮሪደርና ሌሎች የልማት ስራዎች የከተማዋን ገፅታ በእጅጉ እየቀየሩ ይገኛሉ።

‎የኮሪደር ልማቱ ከጣና ኃይቅ ዳርቻ ጋር ተሳስሮ መልማቱ የከተማዋን ውበት ይበልጥ እንዲገለጥ በማድረጉ የቱሪስቶች መዳረሻ ማዕከል እንድትሆን ማስቻሉን ተናግረዋል።

የከተማው የልማት ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መደረጉ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው÷ ‎በቀጣይም የመኖሪያ ቤት ልማት እንዲስፋፋ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻልና ሌሎች ሕዝቡ ያነሳቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራም ሃሳብ አንስተዋል።

አቶ አዲሱ አረጋ በበኩላቸው÷ ባሕር ዳር ለሌሎች ከተሞች ምሳሌ ልትሆን በሚያስችል አስደማሚ የለውጥ ጎዳና ላይ የምትገኝ ከተማ መሆኗን ገልጸዋል።

‎ከተማዋ በተፈጥሮ የተቸራትን ፀጋ ይበልጥ በኮሪደር ልማት አጉልቶ ለማውጣት የተደረገው ጥረት ከተማዋ ዋነኛ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን አስችሏታል ብለዋል።

‎እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለቱሪዝም መነቃቃት እንዲፈጠርና ገፅታዋ እንዲቀየር ያስቻሉ መሆናቸውን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!