አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት በኦልድትራፎርድ ቦርንማውዝን ያስተናግዳል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ የምሽቱን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ነጥቡን 28 በማድረስ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 5ኛ ላይ ይቀመጣል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች በፕሪሚየር ሊጉ እርስ በእርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
ቦርንማውዝ ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ፥ በሁለቱ ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል፡፡