አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋይዳ መታወቂያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት ትልቅ አቅም ይፈጥራል አሉ የብሔራዊ መታወቂያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ፡፡
ፋይዳ ለሴቶች ንቅናቄ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
አቶ ዮዳሔ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቱ ተደራሽ የመሆን እና የመታወቅ መብትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ሴቶችም ይህን መብታቸውን እንዲጠቀሙ ዕድል የሚሰጥ ነው፡፡
ፋይዳ መታወቂያ ዲጂታል በሆነ መንገድ አገልግሎቶችን ለማግኘት፣ ግብይት ለመፈፀምና የተለያዩ ተግባራትን ለመከወን አስቻይ ሁኔታ እንደሚፈጥር አስረድተዋል፡፡
የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ሂክማ ኬይረዲን በበኩላቸው÷ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቱ ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ መብት መረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡
የማንነት ማጭበርበርን በማስቀረት በሕግ ፊት የመታወቅ እና ነገሮችን በራስ አቅም ለመከወን ለሴቶች ዕድል ይሰጣልም ነው ያሉት፡፡
በመድረኩ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚዎች 40 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን÷ እስከ ሰኔ 30 ድረስ የሴቶችን ቁጥር 30 ሚሊየን ለማድረስ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በወንድሙ አዱኛ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!