አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡ 45 የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች የዕውቅና ሠርቲፊኬት ሰጥቷል።
ለታዛቢዎቹ ዕውቅናው የተሰጠው ቦርዱ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ሲሆን፤ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡና መሥፈርቱን ላሟሉ 45 የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች የዕውቅና ሠርቲፊኬት መስጠቱ ተገልጿል።
ቦርዱ ቀደም ሲል 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች፤ የታዛቢዎችን የምዝገባ ሂደት ቀልጣፋ መረጃ አደረጃጀቱንም ዘመናዊ እንዲያደርግ ታስቦ የተዘጋጀው “የበይነ-መረብ ላይ ምዝገባና መረጃ አደረጃጀትን” አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠቱን አስታውሷል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!