አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ወጣቶች ፎረም 2025 በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በፎረሙ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰለሞን ሶካ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ከ300 በላይ ወጣቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።
ሚኒስትር ዴዔታው በወቅቱ እንዳሉት፥ የወጣቶችን አቅም ማሳደግ ለቀጣይ ትውልድ ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ነው።
ኢትዮጵያ ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑን አስረድተዋል።
የወጣቶችን የሥራ ፈጠራ አቅም ለማሳደግ የተለያዩ ኢኒሼቲቮች ተቀርጸው እየተተገበሩ እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ ለአብነትም የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወጣቶች በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን ክህሎት በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል።
በመደመር ፍልስፍና ወጣቶች በአመራር ሰጪነት፣ በሥራ ፈጠራ፣ በኢንተርፕርነርሽፕና ሌሎች መስኮች ያላቸውን ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
በኔዘርላንድስ ልማት ድርጅት (ኤስኤንቪ) የኢትዮጵያ ተወካይ ጁሊ ግራሃም በበኩላቸው፥ የወጣቶችን ዘርፈ ብዙ አቅም ለማጎልበት በትብብር መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ድርጅቱ የአፍሪካ ወጣቶች በፖሊሲ፣ በኢኖቬሽን፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
እንደራስ የወጣቶች ማህበር እና ኤስኤንቪ በጋራ ያዘጋጁት ፎረሙ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!