ስፓርት

ኢትዮጵያ 5ኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ እንድታዘጋጅ ተመረጠች

By Adimasu Aragawu

December 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎ኢትዮጵያ 5ኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡

‎4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ እየተደረገ በሚገኝባት አንጎላ ሉዋንዳ ከተማ በተደረገ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ውድድሩን የማዘጋጀት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ‎ ‎የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ኢትዮጵያ 5ኛውን የወጣቶች ኦሊምፒክ ጨዋታ በማዘጋጀት ዙሪያ ለጠቅላላ ጉባኤው ንግግር አድርገዋል። ‎ ‎ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸውም የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ይህንን ትልቅ አሕጉራዊ ውድድር ለማዘጋጀት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አብራርተዋል፡፡ ‎ ‎በጥያቄው መሠረትም ጠቅላላ ጉባኤው የኢትዮጵያን የማዘጋጀት ጥያቄ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

በሙባረክ ፋንታው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!