በአዲስ አበባ ከተማ ዘመኑን የዋጀና ቀልጣፋ የትራንስፖራት አማራጭን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ፡፡
በተሳፋሪዎች እና አሽከርካሪዎች የዋጋ ስምምነት የሚመራ ዶንኪይ ድራይቭ የተሰኘ ሜትር ታክሲ አገልግሎት መተግበሪያ ይፋ ተደርጓል፡፡
በመርሐ ግብሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም የሥራ መውጫ እና መግቢያ ሰዓት ላይ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ አዳዲስ አማራጮችን ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የመዲናዋ ትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል፡፡
ዶንኪይ ድራይቭ ሜትር ታክሲ አገልግሎትም የዘርፉ ያለውን እጥረት በመገንዘብ አዳዲስ አመራጮችን ማቅረቡ የሚበረታታ መሆኑን አመልክቷል፡፡
መተግበሪያው ለተጠቃሚዎች የፈለጉትን አሽከርካሪ የመጥራት እንዲሁም የጉዞ ማስጀመር እና ማቋረጥ መብት በተሳፋሪው የመወሰን አማራጭ ይሰጣል፡፡
አምስት የሀገር ውስጥ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎችን የሚጠቀመው አገልግሎቱ÷ ከኦሮሚያ ባንክ ጋር በመተባበር የዲጂታል ብድር አገልግሎት ለአሽከርካሪዎች የሚሰጥበትን አሰራር ማካተቱም ተጠቅሷል፡፡
በተመጣጣኝ ዋጋና በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዘ በሁሉም የኑሮ ደረጃ ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!