ቴክ

ኢትዮጵያና ሩሲያ የኒውክሌር ኃይል ምስጢራዊ መረጃዎችን የመጠበቅ ስምምነት ተፈራረሙ

By Melaku Gedif

December 17, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን እና የሩሲያ ፌዴሬሽን የሮሳቶም ኢነርጂ ፕሮጀክቶች የኒውክሌር ኃይል ሚስጢራዊ መረጃዎችን የመጠበቅ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳንዶካን ደበበ እና የሩሲያ ፌዴሬሽን የሮሳቶም ኢነርጂ ፕሮጀክቶች ዋና ዳይሬክተር አንድሬ ሮዝድስትቪን ናቸው።

በአቶ ሳንዶካን ደበበ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በሩሲያ ሞስኮ ከታኅሣሥ 6 እስከ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሁለቱ ወገኖች የመጀመሪያ ስብሰባ እየተሳተፈ ይገኛል።

በስብሰባው ምስጢራዊ መረጃዎችን የመጠበቅ ስምምነት እና የፍኖተ ካርታ ሰነዶች ለውይይት ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል።

የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ካለው ዓለም አቀፋዊ ውድድር አንጻር ምስጢራዊ መረጃዎች መጠበቅ እንዳለባቸው ተገልጿል።

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኢትዮጵያን የመጀመሪያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ እና ልማት ለማፋጠን ቀደም ብለው የተገቧቸውን ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸው ተነግሯል።

የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል።

መድረኩ ባለፈው መስከረም በሞስኮ ከተካሄደው የዓለም አቶሚክ ሳምንት ጎን ለጎን በተፈረመው አጠቃላይ የተግባር ዕቅድ ላይ ይመክራል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ አገልግሎትና ለኢትዮጵያ አስተማማኝ የኃይል ምንጭ እንዲሆን መጠቀም ላይ መወያየታቸውን የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን አስታውሷል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!