አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር በኮፕ 32 ዝግጅት ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ እና ቡድናቸው ጋር በኮፕ 32 ዝግጅት ዙሪያ ተወያይተናል ብለዋል፡፡
በውይይቱም ኢትዮጵያና የአፍሪካ ህብረት አህጉሪቱን በሚገባ የሚወክል ኮፕ 32 ለማዘጋጀት እንዴት ተቀራርበው መስራት እንደሚችሉ መምከራቸውን ተናግረዋል፡፡
በማህሙድ አሊ ዩሱፍ መሪነት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮፕ 32ን የተሳካ ለማድረግ የኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር ለመሆን ቁርጠኛ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!