የሀገር ውስጥ ዜና

ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና አቶ ተስፋዬ በልጅጌ የመስቀል አደባባይን ፕሮጀክት ጎበኙ

By Tibebu Kebede

August 21, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በመስቀል አደባባይ እየተገነባ ያለውን የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ጎብኝተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በሚፈለገው ፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ አስፈላጊው ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡