ፋና ስብስብ

የፋና ላምሮት ምዕራፍ 21 ስምንተኛ ሳምንት ውድድር ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል

By Yonas Getnet

December 18, 2025

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተወዳጁ ፋና ላምሮት የባለተሰጥዖ ድምፃውያን ውድድር ምዕራፍ 21 ስምንተኛ ሳምንት ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል።

በሳምንቱ የምድብ ሁለት 5 ተወዳዳሪዎች ራሳቸው የመረጧቸውን ሁለት ሙዚቃዎች ከዛየን ባንድ ጋር ያቀርባሉ።

ከተወዳዳሪዎቹ መካከል አንዱ የሚሰናበት ሲሆን አራቱ በቀጣይ ሳምንት ከምድብ አንድ ተወዳዳሪዎች ጋር ይቀላቀላሉ።

ምዕራፉ ለ13 ሳምንታት የሚደረግ ሲሆን በየሳምንቱ ዳኞች በሙያቸው፣ ተመልካቾች ደግሞ ባልተገደበ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ዳኝነት ይሰጡበታል።

በምዕራፉ ፍፃሜ መጨረሻ ላይ የሚቀሩ 4 ተወዳዳሪዎች የአንድ ሚሊየን ብር ሽልማት የሚያሸንፉ ሲሆን፤ አራቱም ተወዳዳሪዎች ወደ 6ኛው አሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ያልፋሉ።

የምዕራፉ ስምንተኛ ሳምንት ውድድር በመጪው ቅዳሜ ቀን ከ6:00 ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት በፋና በሁለቱም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ በፋና ፌስቡክ እና ቴሌግራም ገጾች እንዲሁም በ www.fanamc.com በመከታተል በ8222 አጭር የጽሑፍ መልዕክት የተወዳዳሪዎችን ኮድ በመላክ እየተዝናኑ የዳኝነቱ አካል ይሁኑ።

በለምለም ዮሐንስ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!